(አ.አ.ኢ.ማ)

አዎንታዊ አስተሳሰብ ለኢትዮጵያ ማሕበር

መግቢያ

ይህ አጭር ጽሑፍ የ “አዎንታዊ አስተሳሰብ ለኢትዮጵያ ማሕበር (አአኢማ)” በማህበሩ ውስጥ አባል ለሆኑ እና አባል ለመሆን ለሚፈልጉ ሁሉ የ “አዎንታዊ አስተሳሰብ” ፅንሰ ሀሳብ መገለጫዎቹን እና ጥቅል ትርጓሜን፣ ማሕበሩ በተጨባጭ በዜጎች አብሮ የመኖር ይዘትና ሂደት ውስጥ የሚከተላቸውን መርሆዎችና ዕሴቶችን ይዟል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ “አዎንታዊ አስተሳሰብ” ለአአኢማ አባለት የባህሪ እና የአባልነት መገለጫ ስለመሆኑ በአመላካች ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ይዟል፡:

አዎንታዊ አስተሳሰብ

መገለጫዎች

ራዕይ

በአዎንታዊ አስተሳሰብ መርሆዎች ሁለንተሃዊ ሀገራዊ  ችግሮች እየተፈቱ ፍትሃዊነት፣ አብሮነት፣ ሰላምና ብለፅግና በኢትዮጵየ ሰፍኖ ማየት

ተልዕኮ

በአዎንታዊ የአስተሳሰብና የአመለካከት ለውጥ ላይ በመሥራት ለ21ኛው  ክፍለ ዘመን የሚመጥን ለሀገር ዕድገት የሚተጋ ትውልድን በመቅረጽ የባህል ለውጥ ተመዝግቦ የድህነትና የኃላቀርነት ታሪክን በመፋቅ ሂደት የበኩልን አሻራ ማኖር፡:

ጥቅል መገለጫ

ጠቅለል ባለ ዕሣቤ “አዎንታዊ አስተሳሰብ” ማለት ነገሮችን በቀና መንፈስ ማየት ነው፡፡ ከግለሰብ እስከ ሀገር ጉዳይ የሚፈጠሩ የሃሣብ ልዩነቶችን ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ያለአድልዎ ሁሉንም ሰው ሊያስማማ በሚችል መልኩ በውይይትና በምክክር መፍትሔ ማስገኘት የአዎንታዊ አስተሳሰብ ውጤት ነው፡፡

እሴቶች

አዎንታዊነት ፣ ቅን አሳቢነት፣ ርህራሄ፣ በጐነትና መልካምነት፣

መከባበር፣ መደማመጥ፣ መተሳሰብና ጥምረት በመፍጠር አብሮ ማደግ፣

በግልጸኝነት፣ በትዕግሥተኝነት፣ በአሳታፊነት፣ በምክንያታዊነት እና በሃሣብ አሸናፊነት ማመን

በራስ በመተማመን ልዩነቶችን በማክበርና በሰጥቶ መቀበል መፍታትን ባህላዊ ማድረግ፤

በእውቀትና በእውነት ላይ በመመሰረት በራስ ላብና ሃቅ ብቻ ለመበልጸግ መሥራት ፤

እልኸኝነትን፣ ቂመኝነትን፣ ማጭበርበርን፡ ሙስናን፣ ሌብነትንና አድሎአዊነትን መጠየፍ ፣

ስንፍና እና ልመና አዋራጅ መሆኑን በመገንዘብ አጥብቆ መጥላት፤

ምቀኝነት፣ ራስ ወዳድነት፣ ስግብግብነት፣ ለሀገር ዕድገት እና ሰላም ፀር መሆናቸውን መገንዘብ ፣

Scroll to Top